ነነዌን ሊያቃጥል

ነነዌን ሊያቃጥል የወረደው እሳት
ተመልሶ አረገ በጾምና ጸሎት
ስለሆነ ከልብ የሐዘናቸው ምንጩ
ነበር እንደ ራሄል እንባ እየረጩ
ለነነዌ ሰዎች ደስታን ያበሰረ
ጋሻና ጦራቸው ጾም ፀሎት ነበረ
እንኳን የሰው ልጆች እንስሳት ሳይቀሩ
በዮናስ ስብከት ጾም ፀሎት ተማሩ
← መዝሙር