ነዋ ሚካኤል

ነዋ ሚካኤል መልአከ ክሙ
ይስአል ክሙ በእንተ ምሕረት
መንበሩ ከፍ ያለ ከመላእክት ሁሉ
የምሕረት መልአከ ነው ሚካኤል ኃያሉ
ከጥፋት ያዳነኝ በክንፉ ከልሎ
የጥላትን ምክር ምኞቱን አስጥሎ
የስሙ ትርጓሜ ሚካኤል የሚለው
እንደ እግዚአብሔር ያላ ከአማልክት ማነው
በሰማይ በምድር በባህር በቀላያት
እግዚአብሔር ልዩ ነው የሁላችን አባት
ሚካኤል ሚካኤል የመላእክት አለቃ
ዝምታን አያውቅም ለጥቂት ደቂቃ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አሽናፊ እግዚአብሔር
እያል ይሰግዳል ከሥላሴ መንበር
ክጥንት ጀምሮ በቤቱ አድጌያለሁ
የሚካኤልን ክብር በእውነት አውቀዋለሁ
አበውን የረዳ በኑሯቸው ሁሉ
ዘውትር ይረዳናል ሚካኤል ኃይሉ
← መዝሙር