ንሴብሆ ለእግዚአብሔር

ንሴብሆ ለእግዚአብሔር
ስቡሐ ዘተሰብሐ
እናመስግነው እግዚአብሔርን
ምስጉን ነው የተመሰገነ
ባሕሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍጹም ነጻ ወጣን
ህይወት የሚሰጠን መና ነው ምግባችን
ንሴብሆ ለእግዚአብሔር
ስቡሐ ዘተሰብሐ
እናመስግነው እግዚአብሔርን
ምስጉን ነው የተመሰገነ
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
ንሴብሆ ለእግዚአብሔር
ስቡሐ ዘተሰብሐ
እናመስግነው እግዚአብሔርን
ምስጉን ነው የተመሰገነ
ከዓለት የፈለቀ ውኃ ጠጥተናል
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆኗል
ህዝቦች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
ንሴብሆ ለእግዚአብሔር
ስቡሐ ዘተሰብሐ
እናመስግነው እግዚአብሔርን
ምስጉን ነው የተመሰገነ
← መዝሙር