ንሴብሖ ለሥላሴ

ንሴብሖ ለሥላሴ
ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ
የእኛ አማላጅ እናታችን
ነይ ነይ ወደኛ እመቤታችን
ፈጥነሽ ተገኚ በመሃላችን
ና ወደኛ ሚካኤል
መልአከ ምክሩ ለልኡል
ከእግራችን ይውደቅ ሳጥናኤል
ና ወደኛ ገብርኤል
ከእሳቱ አውጣን ከነበልባል
በክንፍህ ጥላ እንከለል
ና ወደኛ ኡራኤል
እንደ ቅዱስ እዝራ ሱቱኤል
ጥበብን ስጠን ማስተዋል
ና ወደኛ በፈረስ
የልደው ፀሐይ ጊዮርጊስ ገድልህን ሰምተን እንፈወስ
ና ወደኛ ተክለሃይማኖት
ይጠብቀን ያንተ ጸሎት ጸንተን እንድንቆም በሃይማኖት
← መዝሙር