ንጽሕት ድንግል
✦
ንጽህት ድንግል ቡርክት
የአምላክ እናት እመቤት
ልጆችሽ ሙሽሮች ሁለቱም አንድ ሆኑ
ተዋሀዱ ተጣመሩ በቅዱስ ቁርባኑ፪
የአምላክ እናት እመቤት
ልጆችሽ ሙሽሮች ሁለቱም አንድ ሆኑ
ተዋሀዱ ተጣመሩ በቅዱስ ቁርባኑ፪
ፍጹም መንፈሳዊ ልዩ ፍቅር
አንቺ ያለሽበት መልካም ትዳር
መሠረቱ ዛሬ ልጆችሽ
ቅድስት ሆይ ባርኪያቸው ተገኝተሽ
አዝ ---
ድንግል ጐጆአቸውን ቀድሰሽ
እውነተኛ ፍቅር መሥርተሽ
በመካከላቸው ተገኝተሽ
ሁሉን አሰጪያቸው አማልደሽ
አዝ ---
ሙሽሮቹም አምነው በምልጃሽ
እናታችን ባርኪን ነይ ሲሉሽ
ፈጥነሽ ድረሺና በሠርጋቸው
ነይ ተመላለሽ መሀላቸው
አዝ ---
አንቺን ለሚወዱሽ ለሚያምኑሽ
የሕይወት አጣፋጭ ቅመም ነሽ
ሙሽሮቹም ዛሬ ይጠሩሻል
የጐጆዋችን ፋና ነይ ይሉሻል
አዝ ---
ቃና ዘገሊላ ተገኝተሽ
መልካሙን ጋብቻ የባረክሽ
ዛሬም ከልጅሽ ጋር በሠርጋቸው
ነይ ተመላለሽ መሃላቸው
አዝ ---
አንቺ ያለሽበት መልካም ትዳር
መሠረቱ ዛሬ ልጆችሽ
ቅድስት ሆይ ባርኪያቸው ተገኝተሽ
አዝ ---
ድንግል ጐጆአቸውን ቀድሰሽ
እውነተኛ ፍቅር መሥርተሽ
በመካከላቸው ተገኝተሽ
ሁሉን አሰጪያቸው አማልደሽ
አዝ ---
ሙሽሮቹም አምነው በምልጃሽ
እናታችን ባርኪን ነይ ሲሉሽ
ፈጥነሽ ድረሺና በሠርጋቸው
ነይ ተመላለሽ መሀላቸው
አዝ ---
አንቺን ለሚወዱሽ ለሚያምኑሽ
የሕይወት አጣፋጭ ቅመም ነሽ
ሙሽሮቹም ዛሬ ይጠሩሻል
የጐጆዋችን ፋና ነይ ይሉሻል
አዝ ---
ቃና ዘገሊላ ተገኝተሽ
መልካሙን ጋብቻ የባረክሽ
ዛሬም ከልጅሽ ጋር በሠርጋቸው
ነይ ተመላለሽ መሃላቸው
አዝ ---
✦