ቋንቋዬ ነሽ ድንግል

ቋንቋዬ ነሽ ድንግል መግባቢያዬ
መልስ የማገኝብሽ ከጌታዬ
ባንቺ ቀርቤአለሁ ከአምላኬ ፊት
ቤቴ ሞልቶልኛል በበረከት
በምን ስራዬ ነው በፊቱ የቆምኩት
መቼ በቅቼ ነው ስሙን የጠራሁት
አስታራቂ እናት አንቺን ስለሰጠኝ
ስለ ቃል ኪዳንሽ አቤት ልጄ በይኝ
ቅድስና ሕይወት ከኔ ተሰውሮ
በውሸት በሃሜት አንደበቴ ታስሮ
በእመ አምላክ ፍቅር አዲስ ሰው ሆኛለሁ
እንደ መላእክቱ ይኸው እዘምራለሁ
ስለ እማምላክ ብሎ ያፈረ የለም
ባንቺ ያልከበረ ሰው አይገኝም
እንደ ባለማዕረግ እኔም ሰው መባሌ
አንቺን አግኝቼ ነው ድንግል መሰላሌ
ሰላም ለኪ ብዬ ስጀምር ሰላምታን
ሐሴት ይሞላዋል መላው ሰውነቴን
እንደ ቅዱስ ኤፍሬም በምስጋናሽ ልጽና
በእጆችሽ ያለው አምላኬ ነውና
← መዝሙር