ኑ አንቅረብ

ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ
ሥጋውን እንብላ ደሙንም እንጠጣ
የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ተሰውቶልናል እንመገበው
እድፉን ኃጢአታችን በንስሓ አንጽተን
እንቀበልው አምነን በልጅነታችን
አዝ ---
መቅረብ ወደጌታ በእውነት የሚገባው
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱት
ከዋክብት በሰማይ የተነጠፉት
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት
አዝ ---
ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን
ትመግበናለች ሥጋና ደሙን
የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ
ለግብዣ ተጠራን አዋጁ ታወጀ
አዝ ---
መጥቁ ተወለደ እንቅረብ በእልልታ
በኋላ አይረባም ዋይታና ጫጫታ
ይህንን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይበት
አዝ ---
አሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ
የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ
← መዝሙር