ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን
የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን
ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልህ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን
በቃዴስ በረሀ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን
በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን
የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት
← መዝሙር