ኑ እናመስግን
✦
ኑ እናመስግን በዝማሬ በእልልታ፪
ጠላት ዲያብሎስን በሞቱ የረታ
ከኛ ጋር ነውና የሠራዊት ጌታ፪
ጠላት ዲያብሎስን በሞቱ የረታ
ከኛ ጋር ነውና የሠራዊት ጌታ፪
የጨለማ ኑሮ የስደት ሕይወት
በእግዚአብሔር ፍቅር ብርሃን በራበት
ባርነት ቀርቶ ነጻነት ወጣን
ልመናችንን እግዚአብሔር ሰማን
በእግዚአብሔር ፍቅር ብርሃን በራበት
ባርነት ቀርቶ ነጻነት ወጣን
ልመናችንን እግዚአብሔር ሰማን
መሰናክሉን ክፉዉን ፈተና
አልፈነው ወጣን በአምላክ ጎዳና
አምላክ ከኛ ጋር ስለነበረ
ዲያብሎስ አፍሮ ተዋርዶ ቀረ
አልፈነው ወጣን በአምላክ ጎዳና
አምላክ ከኛ ጋር ስለነበረ
ዲያብሎስ አፍሮ ተዋርዶ ቀረ
የሚያስጨንቀኝ ዛሬ ተረታ
የሕዝቡን እንባ አበሰ ጌታ
ባርነት ቀርቶ ስለጎበኘን
አምላካችንን ኑ እናመስግን
የሕዝቡን እንባ አበሰ ጌታ
ባርነት ቀርቶ ስለጎበኘን
አምላካችንን ኑ እናመስግን
✦