ኑ እንቅረብ
✦
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ ፪
ሥጋውን እንብላ፫ ደሙንም እንጠጣ
የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ተሰውቶልናል እንመገበው
እድፉን ኃጢአታችን በንስሓ አንጽተን
እቀበል አምነን በልጅነታችን
መቅረብ ወደጌታ (እግዚአብሔር) በእውነት
የሚገባው
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው
እንቅረብ -----------
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት
ከዋክብት ሰማይ የተነጠፋለት
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት
እንቅረብ --------------
ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን
ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን
የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ
ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ
መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ
በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ
ኑ እንቅረብ ----------------
ይህችን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይበት
ከአሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ
ኑ እንቅረብ ---------------
ሥጋውን እንብላ፫ ደሙንም እንጠጣ
የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ተሰውቶልናል እንመገበው
እድፉን ኃጢአታችን በንስሓ አንጽተን
እቀበል አምነን በልጅነታችን
መቅረብ ወደጌታ (እግዚአብሔር) በእውነት
የሚገባው
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው
እንቅረብ -----------
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት
ከዋክብት ሰማይ የተነጠፋለት
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት
እንቅረብ --------------
ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን
ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን
የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ
ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ
መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ
በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ
ኑ እንቅረብ ----------------
ይህችን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይበት
ከአሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ
ኑ እንቅረብ ---------------
✦