ኑ ተመልከቱልኝ
✦
ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ፪
ኑ ተመልከቱልኝ የእመቤቴን ሥራ
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ፪
ሐናና ኢያቄም በጸሎት ሲተጉ
በፈጣሪያቸው መልካሙን ቢያደርጉ
በቅዱስ ጋብቻ ጸንተው ቢራመዱ
የአምላክን እናት ድንግልን ወለዱ፪
ኑ ተመልከቱልኝ የእመቤቴን ሥራ
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ፪
ሐናና ኢያቄም በጸሎት ሲተጉ
በፈጣሪያቸው መልካሙን ቢያደርጉ
በቅዱስ ጋብቻ ጸንተው ቢራመዱ
የአምላክን እናት ድንግልን ወለዱ፪
ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ ፪
ቀን ከሌት ሲጸልይ ዘካርያስ ካህን
ኤልሣቤጥም ተግታ ፈጣሪን ብትለምን
በእግዚአብሔር ጥበብ በስተእርጅናቸው
ቅዱስ ዩሐንስን አክብሮ ሠጣቸው፪
ኤልሣቤጥም ተግታ ፈጣሪን ብትለምን
በእግዚአብሔር ጥበብ በስተእርጅናቸው
ቅዱስ ዩሐንስን አክብሮ ሠጣቸው፪
ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ ፪
ጸጋ ዘአብና ቅድስት እግዚእ ኀረያ
ለመልካም ጋብቻ ሆነዋል አርዓያ
ተክለሃይማኖትን ጻድቁን ያፈሩት
ቀን ከሌት ተግተው ነው በጾምና ጸሎት፪
ለመልካም ጋብቻ ሆነዋል አርዓያ
ተክለሃይማኖትን ጻድቁን ያፈሩት
ቀን ከሌት ተግተው ነው በጾምና ጸሎት፪
ኑ ተመልከቱልኝ የአማኑኤልን ሥራ ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ ፪
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ ፪
✦