ኦ ድንግል አኮ

ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ
ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሳዶን
አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ
ውስተ ቤተ መቅደስ
ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ
እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያድግሽ
አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ
← መዝሙር