ቃና ዘገሊላ

ቃና ዘገሊላ በዛ በሠርግ ቤት
ተገኝተሻል ድንግል ከልጅሽ ጋራ
ተገኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ
እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙበት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ አልቆበት
ድንግል እናታችን ቤዛዊት ዓለም
አንቺ ደረሽለት ሆነሽው አማላጅ
አዝ ---
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላቸው
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ
ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ
አዝ ---
የጌታ አምላክነት የተገለጸበት
ምንኛ ታደለ የእነዶኪማስ ቤት
ዛሬም ይኸው በዚህ በደብረ ምሕረት
በረከት ፈሠሠ በአምላክ ቸርነት
አዝ ---
ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን
ሁሉ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን
← መዝሙር