ቀኑ መሽቷል ጌታ ሆይ

ቀኑ መሽቷል ጌታ ሆይ
አትሂድ ከኛ ዘንድ ቆይ
እደር ከኛ ጋራ ኤማሁስ
በአንተ ነፍሳችን /ትቀደስ/
ሲቀላቀለን መሀላችን
አልመሠለንም አምላካችን
ለካስ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው
አብሮን ከኛ ጋራ ያለው
አዝ=====
አብሮን ተጓዘ ደሃ መስሎ
መጣ ልጆቹን ተከትሎ
አሜን ሞትን አሸንፏል
መቃብሩ ባዶ ሆኗል
አዝ======
ባርከህ ስትሰጠን ማዕዱን
ሁሉን ተረዳን ምስጢሩን
አገኘን የልብን ሰላም
መልሰን ኢየሩሳሌም
አዝ======
ወደ ኢየሩሳሌም እንመለስ
ከሞት ተነስቷል ጌታ ኢየሱስ
ይውጣ ኤማሁስ ከልባችን
አብረን እንኑር ከአምላካችን
← መዝሙር