ቀስተ ደመናው
✦
የኖ ቃል ኪዳኑ ምልክት ዓርማው
የመዳኑ ምሥጢር የሰላም ተስፋው
እመቤቴ አንቺ ነሽ ቀስተ ደመናው ፪
አንቺ የአሮን በትር ሳይተክሏት ያደገች
የማክሰኞ እርሻ ያለዘር ያፈራች
የሲና ሐመልማል የተዋሕዶ ምሥጢር
ክብርት እመቤቴ ሀገረ እግዚአብሔር ፪
አዝ . . .
ዳዊት መሰንቆ የያሬድ ጸናጽል
የደኝሞች ምርኩዝ የሰሎሞን አክሊል
ሰላሜ ተስፋዬ የሐዘኔ ደራሽ
የጽዮን ተራራ መሸሸጊያዬ ነሽ ፪
አዝ . . .
የኤልሳዕ ማሰሮ ጨው የተገኘብሽ
የሕዝቅኤል ራእይ ንጽሕት አዳራሽ
አንቺ የአዳም ተስፋ የመዳኑ ብሥራት
አንቀጸ ብርሃን ነሽ የአማኑኤል እናት፪
አዝ . . .
የመዳኑ ምሥጢር የሰላም ተስፋው
እመቤቴ አንቺ ነሽ ቀስተ ደመናው ፪
አንቺ የአሮን በትር ሳይተክሏት ያደገች
የማክሰኞ እርሻ ያለዘር ያፈራች
የሲና ሐመልማል የተዋሕዶ ምሥጢር
ክብርት እመቤቴ ሀገረ እግዚአብሔር ፪
አዝ . . .
ዳዊት መሰንቆ የያሬድ ጸናጽል
የደኝሞች ምርኩዝ የሰሎሞን አክሊል
ሰላሜ ተስፋዬ የሐዘኔ ደራሽ
የጽዮን ተራራ መሸሸጊያዬ ነሽ ፪
አዝ . . .
የኤልሳዕ ማሰሮ ጨው የተገኘብሽ
የሕዝቅኤል ራእይ ንጽሕት አዳራሽ
አንቺ የአዳም ተስፋ የመዳኑ ብሥራት
አንቀጸ ብርሃን ነሽ የአማኑኤል እናት፪
አዝ . . .
✦