ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ
✦
ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ
ወንጌልን አስተምሩን መጥታችሁ በመንፈስ
ክህደት ስለበዛ ባለንበት ዘመን
ቅዱሳን ሐዋርያት እምነትን አሰጡን፪
ወንጌልን አስተምሩን መጥታችሁ በመንፈስ
ክህደት ስለበዛ ባለንበት ዘመን
ቅዱሳን ሐዋርያት እምነትን አሰጡን፪
ቃሉን እንዳንሰማ መልእክቶቻችሁን
በሥጋዊ ፈቃድ ተደፍኗል ልባችን
ማስተዋል አቃተን ነገረ እግዚአብሔርን
ዐይናችን ታወረ እምነት ስለሌለን፪
በሥጋዊ ፈቃድ ተደፍኗል ልባችን
ማስተዋል አቃተን ነገረ እግዚአብሔርን
ዐይናችን ታወረ እምነት ስለሌለን፪
ከሃዲያን በዝተው ባለንበት ዓለም
ልባቸው ተደፍኗል ወንጌል በማጣመም
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ክህደቱን አጥፉልን እንድንደን በነፍስ፪
ልባቸው ተደፍኗል ወንጌል በማጣመም
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ክህደቱን አጥፉልን እንድንደን በነፍስ፪
ክህደትን ያውጃል አውሬው አንደገና
በእምነት እንዳንጸና ሆኖብን ፈተና
እናንተ የጸናችሁ ሰማዕታት በመሆን
ቅዱሳን ሓዋርያት እምነትን አሰጡን፪
በእምነት እንዳንጸና ሆኖብን ፈተና
እናንተ የጸናችሁ ሰማዕታት በመሆን
ቅዱሳን ሓዋርያት እምነትን አሰጡን፪
በጽርሐ ጽዮን ከሐዋርያት ጋራ
የተገነሽ ድንግል አስቢን አደራ
ጽናታችን ሁኚ እንደ ሐዋርያት
ምስክር እንድንሆን ጸንተን በሃይማኖት፪
የተገነሽ ድንግል አስቢን አደራ
ጽናታችን ሁኚ እንደ ሐዋርያት
ምስክር እንድንሆን ጸንተን በሃይማኖት፪
✦