ቅዱሳን ሐዋርያት

ቅዱሳን ሐዋርያት
ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ
ወንጌልን አስተምሩን መጥታችሁ በመንፈስ
ክህደት ስለበዛ ባለንበት ዘመን
ቅዱሳን ሐዋርያት እምነትን አሰጡን
ቃሉን እንዳንሰማ መልእክቶቻችሁን
በሥጋዊ ፈቃድ ተደፍኗል ልባችን
ማስተዋል አቃተን ነገረ እግዚአብሔርን
ዓይናችን ታወረ እምነት ስለሌለን
ከሃዲያን በዝተው ባለንበት ዓለም
ልባቸው ተደፍኗል ወንጌል በማጣመም
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ክህደቱን አጥፉልን እንድንድን በነፍስ
ክህደትን ያውጃል አውሬው እንደገና
በእምነት እንዳንጸና ሆኖብን ፈተና
እናንተ የጸናችሁ ሰማዕታት በመሆን
ቅዱሳን ሐዋርያት እምነትን አሰጡን
በጽርሃ ጽዮን ከሐዋርያት ጋር
የተገኘሽ ድንግል አስቢን አደራ
ጽናታችን ሁኚ እንደ ሐዋርያት
ምስክር እንድንሆን ጸንተን በሃይማኖት
← መዝሙር