ቅያሜው ይቅርና
✦
ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
እስከመቼ ድረስ ሕዝብህ ተጐሳቁሎ
በረከሰ መንፈሰ ለርኩሰት ተጥሎ
ምድር እያለቀሰች ደም እየሸተታት
እባክህ አምላኬ ኢትዮጵያን ታረቃት
እባክህ አምላኬ አገሬን ታረቃት
በረከሰ መንፈሰ ለርኩሰት ተጥሎ
ምድር እያለቀሰች ደም እየሸተታት
እባክህ አምላኬ ኢትዮጵያን ታረቃት
እባክህ አምላኬ አገሬን ታረቃት
ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
የዘመኑ ጣኦት ገንዘብ እያሳተን
ይህ ደካማ ሥጋ አምላክን አስተወን
ግብዝነት ሞልቶት ፈራሹ አካል
በነፍስ በሽታ ሕዝባችን ታሟል፪
ይህ ደካማ ሥጋ አምላክን አስተወን
ግብዝነት ሞልቶት ፈራሹ አካል
በነፍስ በሽታ ሕዝባችን ታሟል፪
ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
ክንፋችን ተመትቶ መብረር አቅቶናል
በመንፈስ በሽታ ሕዝባችን ታዉኳል
ምግባር የጐደለን ተራ ሰዉ ስለሆን
እባክህ ጌታችን በፍጥነት ታረቀን ፪
በመንፈስ በሽታ ሕዝባችን ታዉኳል
ምግባር የጐደለን ተራ ሰዉ ስለሆን
እባክህ ጌታችን በፍጥነት ታረቀን ፪
ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
ጸጋህ የተለየን ባዶነት የመላን
እርቅ የተነፈገን ሰላም የጐደለን
ሆነን ስለቀረን እግዚአብሔር ታረቀን
ጽድቅህን አድለን ጽድቅን ለተመኘን
እርቅ የተነፈገን ሰላም የጐደለን
ሆነን ስለቀረን እግዚአብሔር ታረቀን
ጽድቅህን አድለን ጽድቅን ለተመኘን
ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን
✦