ርግብና ዋኔን

አብረው ዘመቱና ዋኔን
ርግብ ደህና ገባች “
ዋኔን ገደሉና “
ልጆችሽን ባርኪ ዋኔን
ዘወትር ጠዋት ማታ ዋኔን
ዓለም እንዳትጥለን ዋኔን
ወደ እርሷ ጐትታ ዋኔን
የተሰጠሽ ኪዳን ዋኔን
ጸጋ በረከቱ ዋኔን
እንዳንርቅ ያደርገን ዋኔን
ዘለዓለም ከቤቱ ዋኔን
ፀሐይ በመስኮቷ ዋኔን
ስትወጣ እያያችሁ ዋኔን
እንዳትታለሉ ዋኔን
ቀን ያለ መስሏችሁ ዋኔን
ከሰማዩ ችሎት ዋኔን
ሲጠራኝ ጌታዬ ዋኔን
ምን ይዤ እቀርብ ይሆን ዋኔን
አወይ መከራዬ ዋኔን
የሚያመሰግኑሽ ዋኔን
መላእክት በራማ ዋኔን
ጠላትም ይርዳል ዋኔን
የአንቺን ስም ሲሰማ ዋኔን
ቀድሞ እንደነገረን ዋኔን
አባ ሕርያቆስ ዋኔን
ምሳሌ የለሽም ዋኔን
እመ ክርስቶስ
አየሁን በሕልሜ ሞት የተማለውን
ሥጋ ተሸክሜ
ሰማሁት በዝና
ቀጠሮ አክባረ ነው ሞት ኣይቀርምና
ባዶ ቢሆን ቤቴ ዋኔን
እኔ እጠራሻለሁ ዋኔን
በረከቴ እነደሆንሽ ዋኔን
እመሰክራለሁ ዋኔን
ማድጋውን መሙላት ዋኔን
ልጅሽ ይቻለዋል ዋኔን
አይኖቼ ስላዩ ዋኔን
ልቤ ያመሠግናል ዋኔን
ነይ ከልጅሽ ጋር ዋኔን
ድንኳንም ጉብኚ ዋኔን
በኃጢኣት የደከመ ዋኔን
መንፍሴን አጽናኚ ዋኔን
በእጅሽ መባረክ ዋኔን
ለእኔ ይገባኛል ዋኔን
ፍቅርሽ የልብ ደስታ ዋኔን
ሐሴት ይሆነኛል ዋኔን
አየሁን በሕልሜ
ሞት የተማለውን ሥጋ ተሸክሜ
ሰማሁት በዝና
ቀጠሮ አክባረ ነው ሞት ኣይቀርምና
← መዝሙር