ርኅሩኅ መልአክ

ሩኅሩኅ መልአክ ነህና ለሁሉ የምትራራ
ገብርኤል አዛኙ እንተ አውጣን ከመከራ
የሚያሳድዱኝ ገብርኤል ሲቆሙ ከፊቴ
ጋሻ ይሆነኛል ገብርኤል ›› ጠባቂው አባቴ
እሳተ ነበልባል ገብርኤል›› ኃያል መልአክ ነህ
ስምህን ሲጠሩ ›ገብርኤል› ፈጥነህ ትደርሳለህ
.................................................... - 131 -
አዝ ------
በራማ የምትኖር ገብርኤል የመላእክት አለቃ
አብሣሪ መልአክ ነህ ›ገብርኤል› የእኛ ዋስ ጠበቃ
ቂርቆስ እናቱን ገብርኤል›› አንተ አዳንካቸው
ከእግዚአብሔር ተልከህ ›› ከሞት ሠወርካቸው
አዝ ---------ገብርኤል
ለእነ ሚሳኤል ገብርኤል ለእነ አናንያ
ረዳት ሆንካቸው ገብርኤል›› ለእነ አዛርያ
ለኛም መድኃኒት ነህ ገብርኤል›› በእምነት ለለመንህ
ሁሌ ትደርሳለህ ›ገብርኤል› በአማላጅነትህ
← መዝሙር