ሣር ቅጠሉ ሰርዶው

ሣር ቅጠሉ ሰርዶው ሰንበሌጥ ቄጠ?ማው
በዚያች ወር በዚያች ቀን ለምልሞ የነበረው
በእልል ዘመሩ በደስ ተሞልተው
ጌ መወለዱን የምሥራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ
ያ ትጉህ እረኛ ሳለ በትጋት
ብርሃንን ለበሰ በእኩለ ሌሊት
ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሠራዊት
ለመመልከት በቃ የጌ ውን ልደት
አዝ ---
የእረኝነት ሥራ ተንቆ እንዲቀር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
አምላክ የመረጠው መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
አዝ ---
የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌ ተወለደ የምሥራች በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉሥ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ
አዝ ---
የሩቅ ምሥራቅ ሰ−ች ሰብአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው
ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
እንደየሥርዓቱ እጅ መንሻ ሰጡ
አዝ ---
ስለተወለደ መድ ን የእኛ ተስፋ
በደል ተወገደ ኃጢአትም ጠፋ
← መዝሙር