ሰብህዎ ለአምላክነ

ሰብህዎ ለአምላክነ
ሰብህዎ ለአምላክነ ሃሌ ሉያ ለእግዚአብሔር
በሰማይ በምድር
ሰማዩን ያልምሶሶ አጽንቷል በቃሉ
መሬትን በውሆች መሃል መስርቷል ድንበሩን
ይታያል ያበራል ጌታ ዛሬም በስራው
ምስጉን ነው ሰራዊት ሁሉ ያመሰገነው
አዝ...
ምህረቱ ይቅርታው ብዙ ከወሰን የሰፋ
አባት ነው ብርቱ መጠጊያ የሰው ልጆች ተስፋ
መጋቢ ለፍጥረት ዓለም ታላቅ ባለጸጋ
ያብባል ይለመልማል እርሱን የተጠጋ
አዝ...
ተመስገን ተመስገን ይላል የተጎበኘ ሰው
ከጥፋት ከጉስቁልና ከሞት የመለሰው
ይቀባል ከታች አንስቶ ከረኝነት ቦታ
ይቅርታው ጸጋው ብዙነው ምህረቱ የጌታ
አዝ...
መላእክት በላይ በሰማይ ይዘምሩለታል
ዳዊትም ከበገናው ጋር በቅኔ ተነስቷል
በምድርም እኛ ልጆቹ እንበል ንሴብሆ
ይገባል ለአምላከ እስራኤል ውዳሴ አምሆ
← መዝሙር