ሰላም ለኪ

ሠላም ለኪ ለኖኅ ሐመሩ
ሠላም ለኪ ለአሮን በትሩ
ሠላም ለኪ ለቅዱስ ዳዊት መሰንቆ መዝሙሩ
ሠላም ለኪ ለጌዴዎን ፀምሩ
ሠላም ለኪ የሰሎሞን መንበረ ክብሩ
ሠላም ለኪ ለፍሬ ስብሐት መጾሩ /2
እመ እግዚአብሔር ፀባኦት ሰላም ለኪ
ሠላም ለኪ ሰረገላሁ ለአሚናዳብ
ሰላም ለኪ መና ያለብሽ ንጹሕ መሶብ
ሰላም ለኪ ያእቆብ ያየሽ በሎዛ
የይስሐቅ መዓዛ
እንዘ ንሴፎ ለበረከትኪ ዘምስለ
አምኃ ንሰግድ ለኪ
ሠላም ለኪ ኅብስተ መና ዘእስራኤል
ሠላም ለኪ የሰማእታት ንጹሕ አክሊል
ሠላም እፀ ጳጦስ ዘሲና
ሰላም ለኪ የኤልያስ መና
እንዘ ንሴፎ ለበረከትኪ ዘምስለ
አምኃ ንሰግድ ለኪ
← መዝሙር