ሰላሜ ባንተ
✦
ሰላሜ ባንተ ነው የኔ ጌታ
እረፍቴ ባንተ ነው የኔ ጌታ
አልከለከል ምስጋና፤
አልከለከል ውዳሴ ላንተ ውለታ (አዝ)
----(አዝ)
ጨለማዬ ባንተ በራልኝ
ከሰው ትከሻ ወረድኩኝ
የምመራበት ዱላዬ
ባንተ ተጥሏል ጌታዬ
አሁን በግላጭ አያለሁ
ሙሉ ሰው በአንተ ሆኛለሁ
----(አዝ)
የመውገሪያው ድንጋይ ቀረልኝ
ጥላቴ በፊቴ አፈረለኝ
በፊትህ አቆምከኝ በፀጋ
ገዝተህኛልና በዋጋ
ለውለታህማ ምን እላለሁ
ተመስገን ብዬ አልፈዋለሁ
----(አዝ)
ሰላላውን ጭን አቅንተሃል
ሽባነቴንም ተርትረሃል
ደካማነቴ ተወገደ
ያክፉ መንፈስ ተሰደደ
ታውጆልኛል ነፃነቴ
አመልክሃለሁ በህይወቴ
----(አዝ)
የአይኔ ላይ ቅርፊት ወለቀ
ሸክሙ ከላዬ ወደቀ
በደማስቆ ብርሃን መታህኝ
የራስህ ምርጥ እቃ አረከኝ
ያከንቱ ድካሜ አለፈ
ልቤ ለፍቅርህ ተሸነፈ
እረፍቴ ባንተ ነው የኔ ጌታ
አልከለከል ምስጋና፤
አልከለከል ውዳሴ ላንተ ውለታ (አዝ)
----(አዝ)
ጨለማዬ ባንተ በራልኝ
ከሰው ትከሻ ወረድኩኝ
የምመራበት ዱላዬ
ባንተ ተጥሏል ጌታዬ
አሁን በግላጭ አያለሁ
ሙሉ ሰው በአንተ ሆኛለሁ
----(አዝ)
የመውገሪያው ድንጋይ ቀረልኝ
ጥላቴ በፊቴ አፈረለኝ
በፊትህ አቆምከኝ በፀጋ
ገዝተህኛልና በዋጋ
ለውለታህማ ምን እላለሁ
ተመስገን ብዬ አልፈዋለሁ
----(አዝ)
ሰላላውን ጭን አቅንተሃል
ሽባነቴንም ተርትረሃል
ደካማነቴ ተወገደ
ያክፉ መንፈስ ተሰደደ
ታውጆልኛል ነፃነቴ
አመልክሃለሁ በህይወቴ
----(አዝ)
የአይኔ ላይ ቅርፊት ወለቀ
ሸክሙ ከላዬ ወደቀ
በደማስቆ ብርሃን መታህኝ
የራስህ ምርጥ እቃ አረከኝ
ያከንቱ ድካሜ አለፈ
ልቤ ለፍቅርህ ተሸነፈ
✦