ሰላምሽ ዛሬ ነው
✦
ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወዳንች መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም[፪]
ወዳንች መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም[፪]
ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በእየሩሳሌም
ሕፃናት በእየሩሳሌም
አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ[፪]
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ[፪]
ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በእየሩሳሌም
ሕፃናት በእየሩሳሌም
ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት
በኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት[፪]
በኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት[፪]
ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በእየሩሳሌም
ሕፃናት በእየሩሳሌም
ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙት
መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት[፪]
መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት[፪]
ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በእየሩሳሌም
ሕፃናት በእየሩሳሌም
የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው[፪]
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው[፪]
ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ
ሕፃናት በእየሩሳሌም
ሕፃናት በእየሩሳሌም
✦