ሴስየነ ሚካኤል

ሴስየነ ሚካኤል
በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ
ሴስየነ ሚካኤል ሕገከ ዘፅድቅ
አንተኑ ሚካኤል መና ዘአውረድከ
ለረዲኦትነ ነዓ ሰአልናከ
በሚፈሩት መሃል የሚሰፍረው መልአክ
መዳን ይወርሱ ዘንድ ለማገዝ የሚላክ
ስመ ትርጓሜሁ መኑ ከመ አምላክ
ዛሬም እንደ ብሉይ መንገዳችንን ባርክ
መና ዘንቦ በሉ ከዐለት ፈልቆ ጠጡ
ጫማቸው አላለቀ ልብስም አለወጡ
ለቀን ፀሐይ ሐሩር ሆኗቸው ደመና
ሌሊት በአምደ ብርሃን የመራቸው ፍና
እንደተናገረው በቅድመ ኢያሱ
ለሰማይ ሠራዊት መልአከ ኃይል እርሱ
ከሰባ ዓመት ቁጣ እያለ ማራቸው
በሰማይ ማለደ በምድር የመራቸው
ዘሴሰይከ መና ለደቂቀ ኅሬ
ለሕዝብህም ልጆች ትቆማለህ ዛሬ
በኃጢአት በረሃ እንዳንቀር ወድቀን
ርስቱን እንድንወርስ ሚካኤል ሆይ እርዳን
← መዝሙር