ሰው ለሰው
✦
ሰው ለሰው ፪ ቢፋቀር ምነው ፪
ለሰው ይመስለዋል ብዙ የሚቆይ
ግን በድንገት ያልፋል ሁሉንም፪ ሳያይ
ሀብትን ከማቻል ቀኑን ሳውቀው
በድንገት ይጠራል፪ አይከተለውም
የሰው ልጅ በተራ መጠራቱ ላይቀር
ምነው አንዱ ለአንዱ መቃብር፪ ባይቆፍር
አይጠቅምም መጨነቅ እንዲያው ለውበት
ይረግፋል ይጠፋል ሁሉም፪ ከመሬት
ዋ ቁንጅና ከንቱ ማማርም ብላሽ
አፈር ትቢያ ሲሆን ሲጨለም፪ሲመሽ
ደሀ ባለጸጋ አንድ ነው መንገዱ
በጨርቅ ተገንዞ በሳጥን፪ መሄዱ
ሰው ዙሪያውን ቢያጥር መዝጊውን ቢሠራ
በሕንፃ ላይ ሕንፃ ቢያስመስል ተራራ
አይቀርም መሄዱ ሁሉም፪ በየተራ
ለሰው ይመስለዋል ብዙ የሚቆይ
ግን በድንገት ያልፋል ሁሉንም፪ ሳያይ
ሀብትን ከማቻል ቀኑን ሳውቀው
በድንገት ይጠራል፪ አይከተለውም
የሰው ልጅ በተራ መጠራቱ ላይቀር
ምነው አንዱ ለአንዱ መቃብር፪ ባይቆፍር
አይጠቅምም መጨነቅ እንዲያው ለውበት
ይረግፋል ይጠፋል ሁሉም፪ ከመሬት
ዋ ቁንጅና ከንቱ ማማርም ብላሽ
አፈር ትቢያ ሲሆን ሲጨለም፪ሲመሽ
ደሀ ባለጸጋ አንድ ነው መንገዱ
በጨርቅ ተገንዞ በሳጥን፪ መሄዱ
ሰው ዙሪያውን ቢያጥር መዝጊውን ቢሠራ
በሕንፃ ላይ ሕንፃ ቢያስመስል ተራራ
አይቀርም መሄዱ ሁሉም፪ በየተራ
✦