ሥላሴ መታመኛዬ

ሥላሴ መታመኛዬ
አምላኬ መጠለያዬ
ጉልበቴ ነህ ማሸነፊያዬ
ሥላሴ መታመኛዬ
ጠፈሩም እርሱ ነው መሠረቱም እርሱ
ፍጥረታት በሙሉ ስሙን አወድሱ
ሱራፌልን ልከህ ከንፈሮቼን ዳሰኝ
ለምጼን ተመልክተህ አምላክ አትጣለኝ (ጌታዬ አትጣለኝ)
አዝ
እንዴት ያለ አንደበት ስምህን ይጠራል
ግርማህን አይቼ ልቤ ተሸብሯል
ዖዝያን አለፈ ክፋቱ እጅግ በዝቶ
አምላኬን አየሁት በዙፋኑ ጸንቶ
አዝ
አልአዛር ያንተ ነው መንገድ የወደቀው
ከእጅህ አላመለጠ ነዌ ባለጸጋው
ነገሥታትም ያንተው በሥልጣን ያሉት
ለስምህ ይንበርከክ ይህ ሁሉ ፍጥረት
አዝ
በድቅድቅ ጨለማ ተስፋ በሌለበት
ብርሃን ሆኖ አየሁት የጌታዬ ምሕረት
ኃይልን ማሸነፍን ጽናትንም ስጠኝ
ጠላት እንዳይጥለኝ ጸጋህን አልብሰኝ
አዝ
← መዝሙር