ሥላሴ ትትረመም

ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ
ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ
ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ
ፍጥረትን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ
/አዝ =====
ልበል ሃሌ ሉያ ኪሩቤልን ልምሰል
በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል
ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሱራፌል
ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል
/አዝ=====
በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል
በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል
ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት
በባሕሪይ እና ደግሞም በመንግሥት
አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት
/አዝ=====
በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ
ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ
ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ጸንቶ
/አዝ=====
ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር
የአምላክ ጌትነት የሥላሴን ክብር
ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ
መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሰጠ
← መዝሙር