ስለ ድንግል ብሎ

ስለ ድንግል ብሎ ኢትዮጵያን ይጎብኛት
ድሮስ ከአምላክ በቀር ይህች አገር ምን አላት
በሠራዊት ብዛት መች ትጠበቃለች
በቅዱሳን ጸሎት እሳት ካልታጠረች
ዓለም ሸምቆባት አህዛብ ይስቃል
በልጆችሽ ዕንባ አውሬው ይቀልዳል
ታልቅ ሕዝብ መሆኑን ማን በነገራቸው
ከዘመናት በፊት አምላክ የጎበኘው
#አዝ
እውነተኛ ዕንባ ፈለቀ ከምድር
በፍጡራን ዋይታ ፍጹም ብትማረር
ዕንባና ደማችን ተደባልቆ ፈሷል
አምላክ ቅጣት ይብቃን አሁን ይቅር በለን
#አዝ
ቅዱሳንን መንቀፍ ወገኔ ተውና
ይልቅ ስለነሱ የጽድቅ ጎዳና
በረድኤታቸው በክብራቸው ጥላ
እንከተላቸው ከፍቅራቸው ኋላ
← መዝሙር