ስምሽ ጣዕም አለው

ስምሽ ጣዕም አለው ኪዳነምሕረት
በላኤሰብእም ይህን አሰበ
ከጥርኝ ውኃ አንጠባጠበ
ልቤ በልጅሽ ላይ ሲያምጽ በጭኝኔ
ይህን ዓለም አይቶ ሲንከራተት ዓይኔ
በልቤ ጽላት ተሣይብኝ
ጣዕምሽ ከዓለም እንዲለየኝ
ጠላት ሲፈትነኝ ሊጥለኝ በሥጋ
በክፋ ምኞቴ ነፍሴ ስትወጋ
እንደ አባቶኟ ልጥራሽ እኔም
ማን አለኝና በዚህ ዓለም
በስምሽ ተማጽነው ነፍሳት ተምረዋል
ከቅዱሳን ዓለም ምሕረት አግኝተዋል
ወደብ ነሽ አንቺ ማረፊያ ቦ
እየወደድኩሽ ልኑር በደስ
← መዝሙር