ታቦር አበራ

ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና
አነቃን ለምስጋና
ሙሴም የቀደመው ሰዉ ኤልያስ ኃይለኛው
ተገኝተዋል በታቦር ምስክርህ ሆነው
እኛም ከገናናው ክብር ያባቱን ቃል ሰምተናል
በረዶ ሆኗል ልብሱ እፁብ እፁብ ብለናል
ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና
አነቃን ለምስጋና
ቃል ገብተህልኝ ነበር ልታሳየኝ ክብርህን
ንገስ ከሞት ገስግሰህ አይቸሃለሁ አሁን
የሳት ፈረሶች አሉህ ታዋጊው የኔ ጌታ
አርሙኒየም ደስ አለው ስሳራን ስለመታ
ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና
አነቃን ለምስጋና
እጠብቅሃለሁኝ በምታልፍበት ቆሜ
መብራቶቼን አብርቼ ነጩን ልብስ ተሸልሜ
የዳዊት ልጆይ ግባ ኢየሱስ ወደቤቴ
ብልኤል እልሀለሁ ድናለች ሰውነቴ
ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና
አነቃን ለምስጋና
ሁሉንም ብታከብር ሁሉንም ብትምረው
ማነው ቸርነትህን የሚከለክለው
ጠዋትም የተጠራ አምሽቶ የገባው
ሆነዋል ባለዋጋ ከበዛው ስጦታው
ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና
አነቃን ለምስጋና
የረዳኸው ይናገራል ያሰበከው በሕይወቱ
አቤነዘር እያለ ይዘምር ባንደበቱ
በደስታየም ቀን አለህ አይሃለሁ ከጎኔ
ከነጋር አልቅሰሃ አሳዝኖህ ሀዘኔ
ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና
እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና
አነቃን ለምስጋና
← መዝሙር