ጠብቀኝ አምላኬ

እንዳልሰናከል ጠብቀኝ አምላኬ
እለምንሀለሁ ደጅህ ተንበርክኬ
እንደ ቃልህ ልኑር አበርታኝ ጌታዬ
ምሕረትህን ስሻ ታጠብኩ በእንባዬ
መሆን በተገባኝ ደጉን አስተማሪ
በጎውን የማሳይ ወደቤትህ መሪ
ፍሬ ያልተገኘባት ባዶ ነው ህይወቴ
እጄን ይዘህ ምራኝ መልሰኝ አባቴ
አዝ.........................
መንገዴን ለውጠው አካሄዴም ይቅና
አብቃኝ ለንስሀ ልይህ እንደገና
በምህረት ቃልህ ልጄ በለኝ ጌታ
አርቀህ ጣልልኝ የእኔን ነቀፌታ
አዝ........................
የመንገድ እንቅፋት እንዳልሆን ጋሬጣ
ቅዱስ መንፈስህን ወደ ልቤ አምጣ
እንዳይሰናከል የሚያየኝ ሰው ሁሉ
ለምለም ቅጠል አድርገኝ የሚያፈራ ተክሉ
አዝ..........................
አንተን ደስ የሚያሰኝ እንዳፈራ ፍሬ
ትርጉሙን እንዲያገኝ በስምህ መኖሬ
እማጸንሃለሁ ይቅር በለኝ ብዬ
እጠበኝ እነፃለሁ እራራልኝ ጌታዬ
አዝ....................
ዘማሪ መምህር ግርማ ባቱ፣ ዲ.ን ዘማሪ ሳምሶን ነጋሽ፣ ለምለም ከበደ
← መዝሙር