ተፈሥኢ

ተፈሥሒ ቤተክርስቲያን ተፈሥሒ ቤተ ሥላሴ
ያሳደግሻቸው ልጆችሽ አብርሃም ሣራን ሲሆኑልሽ
ያሳደግሻቸው ሙሽሮችሽ አብርሃም ሣራን ሲሆኑልሽ
አዝ ---
ትምህርትሽ ገብቶአቸው የወንጌሉ ቃል
በኑሮ ሊያበሩ ይኸው ወጥተዋል
በክርስቶስ ትምህርት በቃሉ ተመርተው
ለዓለም መሠከሩ ተራራ ላይ ቆመው ተፈሥሒ
አዝ ---
ከእንቅቡ በታች አይደለም መብራቱ
በራ እንጂ ለሁሉ ከእነበረከቱ
ጢስ የሌለው ሻማ ደምቀው የከበሩ
ልጆችሽ ሙሽሮች እንደጧፍ አበሩ፡፡ ተፈሰሒ
አዝ ---
ሰላም ላንቺ ይሁን ደስ ይበልሽ በጣም
የዘራሽው ማሳ ፍሬውን ሲሸከም
ካባ ደረብሽለት ለወንዱ ሙሽራ
አክሊል ደፋሸለት ከምርቃት ጋራ ተፈሰሒ
አዝ ---
ቃልሽ ይለውጣል ግሩም ነው ኃያል
አመንዝራዎቹን ድንግል ያደርጋል
ተገለጠ ክብርሽ በሙሽሮች ዛሬ
መከር ሆኖልሻል ባፈራሽው ፍሬ ተፈሥሒ
አዝ ---
ሰላም ላንቺ ይሁን ደስ ይበልሸ በጣም
የዘራሽው ማሳ ፍሬውን ሲሸከም
ካባ ደረብሽለት ለወንዱ ሙሽራ
አክሊል ደፋሸለት ከምርቃት ጋር ተፈሥሒ
አዝ ---
← መዝሙር