ተፈጸመ አለ

ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ
ስለኔ ኃጢአት በመከራ አለፈ
ደፋ ቀና እያለ ሲወርድ ሲንገለታ
ያ ብርሃን ፊቱ በጥፊ ተመታ
በሐሰት ተከሶ በሐሰት ተገደለ
በውርደት ሸንጎ ፊት ባደባባይ ዋለ
በውሀ ጥም ዛለ በረሀብ ተቀጣ
ስለ ሰው ልጆች ሲል የሞት ጽዋን ጠጣ
አንቺ ዕለተ ዓርብ እንዴት ያለሽው ነሽ
ሰማያዊ አባት የተሰቀለብሽ
ከኋላ ከፊቱ በጠላት ተከሶ
ማንም አልነበረም የሚያናናው ከቶ
ርኁሩኅ ጌታዬ ስኔ ብለህ ነው
ያንን ሁሉ መከራ በትዕግሥት ያለፍከው
ዘማሪ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል
← መዝሙር