ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ

ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ
ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ
እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ
ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ
በተዋሕዶ በእምነታቸው ፀንተው
ከንቱውን ነገር ይህችን ዓለም ንቀው
እናታችን ማርያምን ይዘው
ይጓዛሉ ክርስቶስን ለብሰው
ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ
ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ
እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ
ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ
ተሳፍረዋል በአንዲቱ እምነት
በጥንቲቱ ጽኑ ሃይማኖት
አንድ ናቸው ማንም አይለያቸው
ያኑራችሁ በእምነት ጸንታችሁ
ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ
ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ
እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ
ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ
የክብር አክሊል እንድትቀዳጁ
ኢየሩሳሌም ትሁን ርስታችሁ
እግዚአብሔር አምላክ ፍቅርን ይስጣችሁ
ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ
ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ
እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ
ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ
← መዝሙር