ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
✦
የጽድቅ ፀሀይ አዲስ ሃዋርያ
ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
ደብረ ሊባኖስ ላይ አጽምህ አርፏል በክብር
ድንቅን ይፈጽማል እየሰራ ተዓምር
አባቴ ልበልህ ቃል ኪዳንህ ፅኑ
ፀበልህ ፈውስ ነው በምልጃህ ላመኑ
አዝ.......................
ከሱራፌል ጋራ በሰማዩ መቅደስ
ዙፋኑን አጥነሃል እያልክ ስሉስ ቅዱስ
ሰይጣንን ያሰርከው በስመስላሴ
መናን የምትመግብ ነህ ዳግማዊ ሙሴ
አዝ.....................
የወንጌሉን ትዕዛዝ ቃሉን የምትፈፅም
የእምነት አርበኛ ብርሃን ነህ ለዓለም
ሰፍቷል እንደ ዋርካ ዝናህ እጅግ በዝቶ
በሽተኛው ድኗል ፀበልህን ጠጥቶ
አዝ........................
መንገዴ ይቀናል ስምህን ስጠራ
ገድልህ ሲተረጎም ሸሸ የሞት ጭፍራ
ባርከኝ በመስቀልህ ተክለሃይማኖት
አድነኝ ከሲኦል ከዳግመኛ ሞት
አዝ......................
ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
ደብረ ሊባኖስ ላይ አጽምህ አርፏል በክብር
ድንቅን ይፈጽማል እየሰራ ተዓምር
አባቴ ልበልህ ቃል ኪዳንህ ፅኑ
ፀበልህ ፈውስ ነው በምልጃህ ላመኑ
አዝ.......................
ከሱራፌል ጋራ በሰማዩ መቅደስ
ዙፋኑን አጥነሃል እያልክ ስሉስ ቅዱስ
ሰይጣንን ያሰርከው በስመስላሴ
መናን የምትመግብ ነህ ዳግማዊ ሙሴ
አዝ.....................
የወንጌሉን ትዕዛዝ ቃሉን የምትፈፅም
የእምነት አርበኛ ብርሃን ነህ ለዓለም
ሰፍቷል እንደ ዋርካ ዝናህ እጅግ በዝቶ
በሽተኛው ድኗል ፀበልህን ጠጥቶ
አዝ........................
መንገዴ ይቀናል ስምህን ስጠራ
ገድልህ ሲተረጎም ሸሸ የሞት ጭፍራ
ባርከኝ በመስቀልህ ተክለሃይማኖት
አድነኝ ከሲኦል ከዳግመኛ ሞት
አዝ......................
ዘማሪ ቀሲስ ብሩክ አስማረ
✦