ተነግሮ የማያልቅ

ተነግሮ የማያልቅ ነው ጸጋህ
በጸሎት የተጋህ የሃይማኖት ፍሬ
ተክለ ሃይማኖት የወንጌል ገበሬ
አዝ -----------------------
በወንጌል ብርሃን ሕዝቡን የመራኸው
የኃጢአቱን ባሕር ከፍለህ ያሻገርከው
ኢትዮጲያዊው ሙሴ በመስቀልህ ባርከን
ፍሬ እንድናፈራ ንጹሕ አድርገን
አዝ --------------------
ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለሃይማኖት
ወንጌል ያስተማርከው ለክርስቶስ መንግሥት
ጠበልህ እንድምረን ውረድ አባታችን
በእጣንህ መኣዛ ይፈወስ ደዌአችን
አዝ --------------
ለማጠን የበቃህ የሥላሴን መንበር
ሰይጣን ከቶም አይደርስ በሄድክበት ሀገር
ለህሙማን ሁሉ የሆነካቸው ፈውስ
ጠብቀን አቡዬ በሥጋም በነፍስ
አዝ---------------
በጣሙን የበዛ ትሩፋት ምግባርህ
ጸሎትህን ያልተውክ ቢቆረጥ አንድ እግርህ
ምእራፈ ቅዱሳን የወንጌል ገበሬ
እኛንም አድነን ከዘህ ኣለም አውሬ
አዝ ---------------------
← መዝሙር