ተቀበል ምስጋናዬ

እንባዬ ከዓይኔ ደርቋል በሳቅ ተሞልቷል አፌ
ማዕበሉን ሞገዱን በአንተ ፈቃድ አልፌ
መከራን አስረስተህ ካቀለልከው ሸክሜ
ይድረስህ ውዳሴ ተቀበል ምስጋናዬ
ስማፀንህ ነበረ የእንባ መባ ይዤ
በብርቱ ሰልፍ ደክሜ በመከራ ፈዝዤ
ተረት ሆኖ አልፎልኝ ያ ሁሉ የለም አሁን
ስላልተውከኝ ጌታዬ ስለስምህ ክብር ይሁን
አዝ.....................
በምስጋና ተባርኬ ዘወትር ስምክን እጠራለሁ
ከእቅፍህ ሳልወጣ በድንኳንህ እኖራለሁ
እገልጣለሁ በበገና ክብርህን በአዲስ ቅኔ
ቀኔም በቤትህ ይለቅ ያንተ ይሁን ዘመኔ
አዝ..................
ዐይኖቼ እረፍትን አጥተው ትራሴም በእንባ እርሷል
ነፍሴን ተፀይፌአለሁ አጥንቶቼ ደክመዋል
ያን ክፉ ቀን የማልፈው አይመስለኝም ነበር
አሁን ግን አመለጥኩኝ ወጥመዱ ተሰበረ
አዝ................
በበደሌ ሳትፈርድ በድካሜ እራርተህ
ሙሉ ሠው አድርገህኛል የቤቴ ራስ ሆነህ
በወደድከኝ አባቴ በአንተ ተባርኬያለሁ
ብቻዬን አይደለሁም እልፍ ሆኜ በዝቻለሁ
አዝ..................
ዘማሪ ሲሳይ ወልደአረጋይ፣ ለምለም ከበደ
← መዝሙር