ተወዳጅ ልጅሽ

ተወዳጅ ልጅሽ ህማሙን ሲታይ
ማሰብ ይሳነኛል የአንቺን ስቃይ
በሾህ አክሊል ጉንጉን የቆሰለ እራሱን
በብዙ ግርፋት የታመመ አካሉን የታመመ አካሉን
በእፀ መስቀሉ የወረደ ደሙ
የቀራኒዮ ግፍ እጅግ ማስገረሙ
ደጉ ልጅሽ ታስሮ የፍጥኝ ሲሰቃይ
ተሰክቶ ቀረ አይንሽን ወደ ሰማይ
ስለ መሰቀሉ አይሁድ ሲደሰቱ
ሲስቁ ሲያሾፉ ቁማር ሲጨወቱ
ሲዘባበቱበት አይንሽ በማየቱ
ህሊናሽ ተገርፏል በሀዘን በብርቱ በሀዘን በብርቱ
ብላይቴናይቱ የዳዊት ልጅ ማርያም
ስለደረሰብሽ ቢነገር አያልቅም
ተጠማሁ ቢላቸው መፃፃ አስጎነጩት
መርገም አስወገዶ ቢሰጣቸው ህይወት ቢሰጣቸው ህይወት
ለመጠጡ እንዲሆን መፃፃ ከሀሞት
ሰፍነግም ጨምረው በዘንግ አስጎነጩት
ዳዊት በትንቢቱ እንደተነበየው
በምግቤ መራራን ጨመሩ እንዳለው ጨመሩ እንዳለው
ይሄ ሁሉ ሲሆን ድንግል ተመልክታ
መፅናናት ተሳናት በሀዘን ተነክታ
ኤሎሄ ጌታ ባለ ጊዜ
እጅግ ኃያል ነበር የማርያም ትካዜ የማርያም ትካዜ
ተወዳጅ ልጅሽ ህማሙን ሲታይ
ማሰብ ይሳነኛል የአንቺን ስቃይ
በሾህ አክሊል ጉንጉን የቆሰለ እራሱን
በብዙ ግርፋት የታመመ አካሉን የታመመ አካሉን
← መዝሙር