ተወለደ ጌታ ተወለደ

ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ
አንዲት ብላቴና የአስራ አምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ
በኅቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ
አዝ.................................
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ
አዝ.................................
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማኅጸንሽ ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ አዝ.................................
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንዳንቺ አልተገኘም
በሐሳብ በግብር ንጹሕ ስለሆነች
የአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
አዝ.................................
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማኅጸን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ አዝ.................................
← መዝሙር