ተወለደ
✦
ተወለደ አምላክ ተወለደ
አዝ --------
አንዲት ብላቴና የአሥራ አምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ
በኅቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚድን የሰዎች አለኝታ
አዝ--------------
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ
አየነው አምላክን ከድንግል ተወልዶ
አዝ -----------------
ፍጹም ድንግልና ክብርን የተመላሽ
እንደምን አምላክን በማሕፀን ያዝሽ
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ
አዝ --------------------
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንደአንቺ አልተገኘም
በሐሰብ በግብር ንጹሕ ስለሆነች
ለአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
አዝ --------
አንዲት ብላቴና የአሥራ አምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ
በኅቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚድን የሰዎች አለኝታ
አዝ--------------
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ
አየነው አምላክን ከድንግል ተወልዶ
አዝ -----------------
ፍጹም ድንግልና ክብርን የተመላሽ
እንደምን አምላክን በማሕፀን ያዝሽ
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ
አዝ --------------------
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንደአንቺ አልተገኘም
በሐሰብ በግብር ንጹሕ ስለሆነች
ለአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
✦