ትኅትናሽ ግሩም ነው

ትኅትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም
እናቱ ሆነሻል ለመድኃኔዓለም
ንጽሕት ስለሆንሽ….. እመቤቴ
እንከን የሌለብሽ ……እመቤቴ
የፍጥረታት ጌታ……. እመቤቴ
በአንቺ ያደረብሽ……. እመቤቴ
የድንግል መመረጥ …..አምቤቴ
ዜናው አስገረመኝ……. እመቤቴ
እሳቱን ታቀፈች ……እመቤተ
የማይቻለውን …….. እመቤቴ
ምርኩዜ ልበልሽ…………እመቤቴ
ጥላ ከለላዬ እመቤቴ
ጋሻዬ ነሽ አንቺ እመቤቴ
ለእኔ መመኪያዬ
በዓለም አንዳልጠፋ እመቤቴ ሕይወቴ መሮብኝ እመቤቴ
እንደ ወይን አጣፍጭው እመቤቴ
ማርያም ድረሽልኝ እመቤቴ
የምሥራቅ ደጃፍ ነሽ እመቤቴ
የሁላችን ደስታ
እሙ ለፀሐየ ጽድቅ እመቤቴ
የሁሉ ጠበቃ እመቤቴ
ድንግል የድል አክሊል እመቤቴ
ድንግል የጽድቅ ሥራ
ድንግል መሰላል ነሽ እመቤቴ
የተዋሕዶ ተስፋ እመቤቴ
← መዝሙር