ትምክተ ዘመድነ
✦
ትምክተ ዘመድነ ፪ ማርያም እምነ
ማርያም ትምክተ ዘመድነ፪
ማርያም ትምክተ ዘመድነ፪
የድኅነታችን አርማ የነፃነታችን
የሕይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን
አንቺን ለኛ ዘር ባያስቀር
እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር
ሁላችንም በጠፋን ነበር
አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ አምላክ ያደረብሽ
የጌድዮንም ፀምር ለይቶ ያከበረሽ
የእኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ
የዋህ ርግብ ከአበው ስር የተገኘሽ
ዕፀ ሳቤቅ የሕይወት ሐረግ ነሽ
አዝ
አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይህችን ዓለም ቢቃኝ
ንጽህት ቅድስት ሆነሽ ማርያም አንቺን ቢያግኝ
ትኅትናሽን ሕይወትሽንም ወዶ
ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ
አከበረሽ በፍጹም ተዋሕዶ
አዝ
የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም
ከኃጥያት ከመርገም የዳነብሽ ዓለም
አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን
በሲዖል ውስጥ ተግዘን የኖርን
ድንግል ባንቺ ነጻነት አገኘን
አዝ
የሕይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን
አንቺን ለኛ ዘር ባያስቀር
እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር
ሁላችንም በጠፋን ነበር
አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ አምላክ ያደረብሽ
የጌድዮንም ፀምር ለይቶ ያከበረሽ
የእኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ
የዋህ ርግብ ከአበው ስር የተገኘሽ
ዕፀ ሳቤቅ የሕይወት ሐረግ ነሽ
አዝ
አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይህችን ዓለም ቢቃኝ
ንጽህት ቅድስት ሆነሽ ማርያም አንቺን ቢያግኝ
ትኅትናሽን ሕይወትሽንም ወዶ
ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ
አከበረሽ በፍጹም ተዋሕዶ
አዝ
የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም
ከኃጥያት ከመርገም የዳነብሽ ዓለም
አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን
በሲዖል ውስጥ ተግዘን የኖርን
ድንግል ባንቺ ነጻነት አገኘን
አዝ
✦