ጥምቀተ ባሕር

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዞች ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደ ኋላ
አዝ = = = = =
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና
አዝ = = = = =
ጌታችን ሲጠመቅ በሰላሳ ዓመት
ባህር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ምስጢረ ሥላሴ ታወቀ ተረዳ
አዝ = = = = =
እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የፅድቅ መሰላል ድህነታችን ለኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ
← መዝሙር