ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
✦
ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ ፪ ያሉ
ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ ፪ ያሉ
ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ
የእግዚአብሔር ዐይኖቹ ጻድቃንን ከማየት
ጆሮቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች
በምልጃቸው እንመን አናመንታ በአንዳች
ጆሮቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች
በምልጃቸው እንመን አናመንታ በአንዳች
ጊዜያዊ ፈተና ሳያሰቅቃቸው
እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው
ሰማያዊው ተስፋ ስለሚታያቸው
በመከራ ሁሉ ጸኑ በእምነታቸው
እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው
ሰማያዊው ተስፋ ስለሚታያቸው
በመከራ ሁሉ ጸኑ በእምነታቸው
ኃጥኡ ነዌ እንኳ በሲዖል እያለ
ስለ ወንድሞቹ ምሕረት ከለመነ
እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ
ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ
ስለ ወንድሞቹ ምሕረት ከለመነ
እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ
ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ
ቀዝቃዛ ውሃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም
የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም
ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወንጌል
አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል
የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም
ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወንጌል
አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል
✦