ጻድቁ ሐብተማርያም

ጻድቁ ሐብተማርያም መጥተናል እኛ ልጆችህ
አድነን አውጣን ከፈተና
አልብሰን የብርሃንን ፋና
ፃድቁ - - - ሰባት አክሊላትን
ፃድቁ - - - በራሱ የደፋ
ፃድቁ - - - በጾም በፀሎት ነው
ፃድቁ - - - ሰይጣንን ያጠፋ
ፃድቁ - - - ፅድቅን የታጠቀው
ፃድቁ - - - የእግዚአብሔር አገልጋይ
ፃድቁ - - - ፃድቁ አባታችን
ፃድቁ - - - የኢትዮጵያ ሲሣይ
#አዝ
ፃድቁ - - - የዮስቴና ጸጋ
ፃድቁ - - - የፍሬ ብሩክ
ፃድቁ - - - ለኛ ለልጆችህ
ፃድቁ - - - መመኪያ የሆንክ
ፃድቁ - - - በምልጃህ አድለን
ፃድቁ - - - ፍቅርና ሰላም
ፃድቁ - - - ፃድቁ አባታችን
ፃድቁ - - - ሐብተ ማርያም
#አዝ
ፃድቁ - - - ከሱራፌል ጋራ
ፃድቁ - - - ለማቅረብ ምስጋና
ፃድቁ - - - ፅድቅን ተጎናጽፎ
ፃድቁ - - - ሀብተ ንፅሕና
ፃድቁ - - - በደብረ ሊባኖስ
ፃድቁ - - - ይሰበይ ላይ ያለው
ፃድቁ - - - ፃድቁ አባታችን
ፃድቁ - - - ሐብተማርያም ነው
#አዝ
ፃድቁ - - - ባለመቶ ፍሬ
ፃድቁ - - - ሀብተማርያም
ፃድቁ - - - ቤታችንን ሞላው
ፃድቁ - - - ፍቅርና ሰላም
ፃድቁ - - - ሚስጥርን ተካፈልክ
ፃድቁ - - - ከጽርሐአርያም
ፃድቁ - - - ፃድቁ አባታችን
ፃድቁ - - - ሐብተማርያም
← መዝሙር