ፀሐይ ሐዋርያ

ፈያታዊ ዘየማን መኑ መሀረከ
ወመኑ ነገረከ ታእምር ዘንተ
ነቢያተ ኢሐተትኩ ወሐዋርያተ ኢተሎኩ
አላ ፀሐይ ቀፀበተኒ ሶበ ርኢኩ አመንኩ
ኃይለ መስቀሉ መድኃኒተ ኮነኒ
✦ ✦ ✦
መድኃኒቴ አንተነህ ጠባቂ እረኛዬ
በመስቀልህ ምራኝ አቤቱ ጌታዬ
በመስቀል ከአንተ ጋር አብሮ የነበረው
ገነትን ወረሰ እሱ እንደተመኘው
ነቢያትም ሆኑ ደግሞም ሐዋርያት
ያተን መስቀል ቀድመው ሳይሰብኩት
በመንግሥትህ ጌታ አስበኝ እያለ
ወዳንተ ጸለየ በመስቀል ላይ ሳለ
ወዳንተ ለመነ ምንም ሳይሰለች
የእርሱም ሐዋርያ ፀሐይ ነበረች
ፀሐይም ያን ጊዜ ፈጥና ጠቀሰችው
የገነት ማኅተም ወዲያው ተሰጠችው
ዘማሪ ቅዱስ ያሬድ፣ መዝሙረ ስብሐት
← መዝሙር