ፀሐይ ዘልዳ

ፀሐይ ዘልዳ ኮከብ ዘልዳ
አድነኒ ጊዮርጊስ እሞተ እዳ
ከሰው ወገን ያለ አድነኒ
ልክ እንደአንተ ያለ ››
ሰባት ዓመት ሙሉ ››
መከራን የቻለ አድነኒ ጊዮርጊሰ እሞተ እዳ
አዝ ------------
በምግባር በሃይማኖት አድነኒ
በሚገባ ተጋድለህ ››
.................................................... - 144 -
ሰባት አክሊላትን ››
ጌታ የሸለመህ አድነኒ ጊዮርጊሰ እሞተ እዳ
አዝ --------
ሲበሉ ሲጠጡ አድነኒ
ነገሥታት ከበው ››
በጸሎትህ ጠፋ ››
ወርዶ እሳት በላቸው አድነኒ
ጊዮርጊስ እሞተ እዳ
አዝ -----
ፍጡነ ረድኤት አድነኒ
ጊዮርጊስ ፈጣኑ ››
እኛንም አድነን ››
ከክፉ ሰይጣን አድነኒ
ጊዮርጊስ እሞተ እዳ
አዝ----
በሞተር ቢፈጩህ አድነኒ
ዱድያኖስ ተስፋቶ ››
አሳፈረው እርሱ ››
ከሞት አስነሥቶ አድነኒ ጊዮርጊስ እሞተእዳ
አዝ -----------------
← መዝሙር