ወዳጄ ሆይ

ወደጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ
የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ
የተዘጋች መቅደስ ንጹሕ አዳራሽ
ሕዝቅኤል ያየሽ የምሥራቋ በር
ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር
የልኡል ማደሪያው አማናዊት መቅደስ
ስለንጽሕናሽ ምስጋናን እናቅርብ
አዝ ----
ሁለቱንም የሆንሽ እናትና ድንግል
ማኀደረ መለኮት ወላዲተ ቃል
ያለዘርአ ብእሲ በኅቱም ድንግልና
አምላክን የወለድሽ ሐመልማለ ሲና
አዝ ------
ምሥራቀ ምሥራቃት ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ
ጨረቃን የምታመስይ ፀሐይን የወለድሽ
የማለዳ ብርሃን ለዓይን የምታሣሺ
ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሺሺ
አዝ --------
← መዝሙር